ማርቆስ 4:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍሬው እንደ በሰለም መከር በመድረሱ፣ ሰውየው ወዲያው ማጭዱን አንሥቶ ዐጨዳ ይጀምራል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሷአልና ወዲያው ማጨድ ይጀምራል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰብሉም በደረሰ ጊዜ መከር በመሆኑ ሰውየው ወዲያውኑ ማጭድ ያዘጋጃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍሬ ግን ሲበስል መከር ደርሶአልና ወዲያው ማጭድ ይልካል። |
ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”
ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ዐብረው ይደጉ። በዚያ ጊዜ ዐጫጆቹን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳትም እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ በጐተራዬ ክተቱ እላቸዋለሁ’ አላቸው።”
በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ የያዘውን፣ “ዘለላው ስለ በሰለ፣ ስለታም ማጭድህን ያዝና በምድር ላይ ያሉትን የወይን ዘለላዎች ሰብስብ” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።