ቀድሞት የሚሄደውና ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፤ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “ሆሳዕና በአርያም!”
ማርቆስ 11:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀደሙትና የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ሆሳዕና!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊቱ የቀደሙትና ከኋላው የተከተሉትም በታላቅ ድምፅ፤ እንዲህ ይሉ ነበር፤ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፊት የቀደሙትና ከኋላ የሚከተሉትም ሁሉ፥ “ሆሳዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቀድሙትም የሚከተሉትም “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቀድሙትም የሚከተሉትም፦ ሆሣዕና፤ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ |
ቀድሞት የሚሄደውና ይከተለው የነበረው ሕዝብም እንዲህ እያለ ይጮኽ ነበር፤ “ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ!” “በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!” “ሆሳዕና በአርያም!”
የዘንባባም ዝንጣፊ ይዘው ሊቀበሉት ወጡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ሆሳዕና!” “በጌታ ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው!” “የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው!”
እነርሱ ግን፣ “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” እያሉ ጮኹ። ጲላጦስም፣ “ንጉሣችሁን ልስቀለውን?” አለ። የካህናት አለቆችም፣ “ከቄሳር በቀር ሌላ ንጉሥ የለንም” ብለው መለሱለት።