ማርቆስ 1:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ለምጻም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፣ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ለምጻምም ወደ እርሱ ቀርቦ ከፊቱ በመንበርከክ፥ “ብትፈቅድ እኮ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት ለመነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ለምጻም ወደ ኢየሱስ መጣና በእግሩ ሥር ተንበርክኮ፦ “ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ሲል ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና “ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ፤” ብሎ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምጻምም ወደ እርሱ መጥቶ ተንበረከከና፦ ብትወድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው። |
ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቈዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኵዝ የሚሄድ ዐንካሳ፣ ወይም በሰይፍ ተመትቶ የሚወድቅ ወይም የሚበላው ያጣ ራብተኛ ከኢዮአብ ቤት አይታጣ።”
እግዚአብሔርም ንጉሡን ቀሠፈው፤ እስከሚሞትበትም ቀን ድረስ ለምጽ ነበረበት፤ በተለየ ቤትም ይኖር ነበር። በዚያ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን በኀላፊነት የሚመራውና የአገሩንም ሕዝብ የሚያስተዳድረው የንጉሡ ልጅ ኢዮአታም ነበር።
በዚህ ጊዜ የሚያሠቅቅ የቈዳ በሽታ የያዛቸው አራት ሰዎች በከተማዪቱ መግቢያ በር አጠገብ ነበሩ፤ እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ “እስክንሞት ድረስ በዚህ የምንቈየው ለምንድን ነው?
ሰሎሞንም ርዝመቱ ዐምስት ክንድ፣ ወርዱ ዐምስት ክንድ፣ ከፍታውም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድረክ በውጭው አደባባይ መካከል አሠርቶ ነበር፤ በመድረኩም ላይ ወጥቶ በመቆም በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤
ከዚያ ተነሥቶ መንገዱን ሲጀመር፣ አንድ ሰው ወደ እርሱ እየሮጠ መጣ፤ በፊቱም በጕልበቱ ተንበርክኮ፣ “መልካም መምህር ሆይ፤ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል” አለው።