La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኃጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ “የኃጢአትን ይቅርታ እንድታገኙ፥ ንስሓ ገብታችሁ ተጠመቁ” በማለት በበረሓ እያወጀ መጣ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኀጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

Ver Capítulo



ማርቆስ 1:4
11 Referencias Cruzadas  

“እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ጫማውን መሸከም ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ፣ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ እርሱም በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።


ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በርሱ እጅ ይጠመቁ ነበር።


በመላው ይሁዳ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎችም በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በርሱ እጅ ተጠመቁ።


የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤ ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣


በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ለመጠመቅ ይመጡ ነበር።


ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ የሆነውን ታውቃላችሁ፤


ታዲያ፣ አሁን ምን ትጠብቃለህ? ተነሥተህ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኀጢአትህም ታጠብ።’