ሉቃስ 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውም ዘር ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያል።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋም የለበሰ ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ይይ!’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትድግና ይይ።” |
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።