ሉቃስ 22:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም በነገሩ ተስማማ፤ አሳልፎ ሊሰጣቸውም ሕዝብ የማይገኝበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሺም አለ፤ ሕዝብም ባልተገኘበት ጊዜ አሳልፎ ሊሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በውሉ ተስማምቶ ሕዝቡ ሳያውቅ ኢየሱስን አሳልፎ ለመስጠት ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እሺ አለ፤ ሰው ሳይኖርም እርሱን አሳልፎ ሊሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይሻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሺም አለ፥ ሕዝብም በሌለበት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር። |