ሉቃስ 22:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳም ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደሱ ሹሞች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ተነጋገረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከቤተ መቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ቤተ መቅደስ ዘብ አዛዦች ሄዶ ኢየሱስን እንዴት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄዶም ከካህናት አለቆችና ከታላላቆች ጋር እርሱን አሳልፎ እንዲሰጣቸው ተነጋገረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄዶም እንዴት አሳልፎ እንዲሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከመቅደስ አዛዦች ጋር ተነጋገረ። |
ከዚያም ኢየሱስ ሊይዙት የመጡትን የካህናት አለቆች፣ የቤተ መቅደስ ሹሞችና ሽማግሌዎችን እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴ እንደሚይዝ ሰው፣ ሰይፍና ቈመጥ ይዛችሁ ወጣችሁን?
የአገልጋዮቹ ሹሙም ከወታደሮቹ ጋራ ሄዶ፣ ይዞ አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን ሕዝቡ በድንጋይ እንዳይወግሯቸው ስለ ፈሩ በኀይል ሳያስገድዱ ነበር።