ሉቃስ 20:44 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ዳዊት እርሱን፣ ‘ጌታ’ ብሎ ሲጠራው እንዴት ልጁ ይሆናል?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ዳዊት እራሱ “ጌታ ብሎ ይጠራዋል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ዳዊት ራሱ ጌታ ብሎ ከጠራው ታዲያ፥ መሲሕ ለዳዊት እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እርሱ ራሱ ዳዊት ‘ጌታዬ’ ያለው እንዴት ልጁ ይሆናል?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ዳዊት፦ ጌታ ብሎ ይጠራዋል፥ እንዴትስ ልጁ ይሆናል? |
አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው! አሜን።
የእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት ምስጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱ በሥጋ ተገለጠ፤ በመንፈስ ጸደቀ፤ በመላእክት ታየ፤ በአሕዛብ ዘንድ ተሰበከ፤ በዓለም ባሉት ታመነ፤ በክብር ዐረገ።
“እኔ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያናት ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፣ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”