በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
ሉቃስ 20:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ስለ ቍጥቋጦ በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ጌታን፣ ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ’ በማለቱ ሙታን እንደሚነሡ ያሳያል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙታን እንደሚነሡ ግን ሙሴ እራሱ በቁጥቋጦው ታሪክ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ’ በማለቱ አስታወቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን፥ ሙሴ ስለ ቊጥቋጦው እሳት በተናገረው ታሪክ ውስጥ፥ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ ጠርቶታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙታን እንደሚነሡስ እግዚአብሔር፦ ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ’ ብሎ በቍጥቋጦው ዘንድ እንደ አነጋገረው ሙሴ ተናግሮአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙታን እንዲነሡ ግን ሙሴ ደግሞ በቍጥቋጦው ዘንድ ጌታን የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ በማለቱ አስታወቀ፤ |
በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
እግዚአብሔርም ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።
ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይሥሐቅ አምላክ ሆይ፤ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤
ደግሞም እግዚአብሔርም ሙሴን፣ “ ‘የአባቶቻችሁ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤’ “ስሜም ለዘለዓለም ይኸው ነው፤ ወደ ፊት በተከታታይ በሚነሣው ትውልድ ሁሉ የምታሰበው በዚህ ስም ነው ብለህ ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው” አለው።
ምድር በምታስገኘው ምርጥ ስጦታና በሙላቷ፣ በሚቃጠለው ቍጥቋጦም ውስጥ በነበረው በርሱ ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፣ በዮሴፍ ዐናት ላይ ይውረዱ።