“ከዚያም ሌላውን፣ ‘አንተስ ስንት አለብህ?’ አለው። “እርሱም፣ ‘ዐምሳ ዳውላ ስንዴ’ አለው። “መጋቢውም፣ ‘የብድር ደብዳቤህን ዕንካ፤ “አርባ ዳውላ” ብለህ ጻፍ’ አለው።
ሉቃስ 20:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ቀጥሎ ሦስተኛ አገልጋዩን ላከ፤ ገበሬዎቹም እርሱንም ደግሞ አቍስለው ወደ ውጭ ጣሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገናም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይኸኛውን ደግሞ አቁሰለው አስወጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ሦስተኛ አገልጋይ ቢልክ እርሱንም ደብድበው አቈሰሉትና አውጥተው ጣሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ ሦስተኛውን አገልጋዩን ላከ፤ እርሱንም አቍስለው ሰደዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጨምሮም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይህን ደግሞ አቍሰለው አወጡት። |
“ከዚያም ሌላውን፣ ‘አንተስ ስንት አለብህ?’ አለው። “እርሱም፣ ‘ዐምሳ ዳውላ ስንዴ’ አለው። “መጋቢውም፣ ‘የብድር ደብዳቤህን ዕንካ፤ “አርባ ዳውላ” ብለህ ጻፍ’ አለው።