እነርሱ ግን የተናገራቸው ነገር አልገባቸውም።
እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም።
እነርሱ ግን እርሱ የተናገረውን አላስተዋሉም።
እነርሱ ግን የነገራቸውን ቃል አላስተዋሉም።
እነርሱ ግን የሚላቸው አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።
ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ የተረዱት አንድም ነገር አልነበረም፤ አባባሉም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለ ምን እንደ ተናገረም አላወቁም።
እነርሱ ግን ይህን አባባል አልተረዱም፤ እንዳያስተውሉ ነገሩ ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህ ነገር መልሰው እንዳይጠይቁትም ፈሩ።