ሉቃስ 18:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህች መበለት ስለምትጨቀጭቀኝ እፈርድላታለሁ፤ አለዚያ ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህች መበለት ስለምታደክመኝ፥ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ፤’ አለ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህች መበለት ስለ ነዘነዘችኝ እፈርድላታለሁ፤ አለበለዚያ ግን ዘወትር እየተመላለሰች ታሰለቸኛለች።’ ” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህቺ ሴት እንዳትዘበዝበኝ፥ ዘወትርም እየመጣች እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ’።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። |
እርሱ ግን አንድም ቃል አልመለሰላትም፤ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው፣ “እየተከተለችን ትጮኻለችና ብታሰናብታትስ?” ብለው ጠየቁት።
በዚያችው ከተማ የምትኖር አንዲት መበለት ነበረች፤ እርሷም፣ ‘ከባላጋራዬ ጋራ ስላለብኝ ጕዳይ ፍረድልኝ’ እያለች ወደ እርሱ ትመላለስ ነበር።