በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን ልጅ አንሥቶ የወፍጮ መጅ ገፊ እስከ ሆነችው እስከ ባሪያዪቱ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኵር ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የቀንድ ከብቱ በኵር በሙሉ ያልቃል።
ሉቃስ 17:35 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለት ሴቶች ዐብረው ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች [ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች፤ ሁለተኛይቱም ትቀራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤ አንድዋ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች። [ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ሴቶችም በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱን ይወስዳሉ፤ ሁለተኛዪቱንም ይተዋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለት ሴቶች በአንድ ወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዲቱ ትወሰዳለች ሁለተኛይቱም ትቀራለች። |
በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን ልጅ አንሥቶ የወፍጮ መጅ ገፊ እስከ ሆነችው እስከ ባሪያዪቱ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኵር ሆኖ የተወለደ ወንድ ልጅ ሁሉ ይሞታል፤ እንዲሁም የቀንድ ከብቱ በኵር በሙሉ ያልቃል።
ከዚያም ፍልስጥኤማውያን ያዙት፤ ዐይኖቹን አውጥተው ወደ ጋዛ ይዘውት ወረዱ፤ በናስ ሰንሰለት አስረውም እስር ቤት ውስጥ እህል እንዲፈጭ አደረጉት።