ሉቃስ 15:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቱም እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፤ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋራ ነህ፤ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ! አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱም እንዲህ አለው፤ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆነ ሁሉ የአንተ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ አንተማ እኮ ዘወትር ከእኔ ጋር ነህ፤ የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ ልጄ ሆይ፥ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፥ ለእኔም የሆነ ሁሉ የአንተ ነው፤ |
እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ።