La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 15:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱም ታናሹ ልጅ አባቱን፣ ‘አባቴ ሆይ፤ ከሀብትህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው፤ አባትየውም ሀብቱን ለልጆቹ አካፈላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱም ታናሹ አባቱን ‘አባቴ ሆይ! ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ፤’ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታናሽዮው አባቱን ‘አባባ፥ ከሀብትህ ከፍለህ ድርሻዬን ስጠኝ’ አለው። ስለዚህ አባትየው ሀብቱን ለሁለት ልጆቹ አካፈለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ታናሹ ልጁም አባ​ቱን፦ ‘አባቴ ሆይ፥ ከገ​ን​ዘ​ብህ የሚ​ደ​ር​ሰ​ኝን ከፍ​ለህ ስጠኝ’ አለው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ከፍሎ ሰጠው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው።

Ver Capítulo



ሉቃስ 15:12
7 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲህ ካሉት ሰዎች በክንድህ አድነኝ፤ ዕድል ፈንታቸው ይህችው ሕይወት ብቻ ከሆነች፣ ከዚህ ዓለም ሰዎች ታደገኝ። ከመዝገብህ ሆዳቸውን ሞላህ፤ ልጆቻቸውም ተትረፍርፎላቸዋል፤ ለልጆቻቸውም ሀብት ያከማቻሉ።


እነዚህ ሁሉ ከተረፈው ሀብታቸው ሰጡ፤ እርሷ ግን ከጕድለቷ ያላትን፣ መኖሪያዋን ሁሉ ሰጠች።”


ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።


“ብዙም ቀን ሳይቈይ፣ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ሁሉ ጠቅልሎ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ በዚያም በማጋጣነት ንብረቱን አባከነ።


ነገር ግን ይህ ልጅህ ንብረትህን ከጋለሞቶች ጋራ አውድሞ ሲመጣ፣ የሠባውን ፍሪዳ ዐረድህለት።’