ሉቃስ 15:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች ሁሉ ሊሰሙት በዙሪያው ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀራጮችና ኃጢአተኞች ሁሉ ትምህርቱን ለመስማት ተሰብስበው ወደ ኢየሱስ መጥተው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀራጮችና ኀጢኣተኞችም ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር። |
“ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።