ሉቃስ 14:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌላው ደግሞ፣ ‘ገና ሙሽራ ስለ ሆንሁ ልመጣ አልችልም’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላውም ‘ሚስት አግብቼአለሁ፤ ስለዚህም ልመጣ አልችልም’ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው ደግሞ ‘ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስለ ሆንኩ ልመጣ አልችልም’ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውም፦ ሚስት አግብችአለሁ፤ ስለዚህ ልመጣ አልችልም በለው አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላውም፦ ሚስት አግብቼአለሁ ስለዚህም ልመጣ አልችልም አለው። |
“ባሪያውም ተመልሶ መጥቶ ይህንኑ ለጌታው ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን፣ ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው አውራ ጐዳናዎችና መተላለፊያ መንገዶች ውጣ፤ ድኾችንና አካለ ስንኩሎችን፣ ዐይነ ስውሮችንና ዐንካሶችን ወደዚህ አስገባቸው’ አለው።
አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፣ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ ቤቱ ይቈይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።