ሉቃስ 11:49 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን እልክላቸዋለሁ፤ እነርሱ አንዳንዶቹን ይገድላሉ፤ ሌሎችንም ያሳድዳሉ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ “ወደ እነርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ትላለች፤ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ አንዳንዶችን ይገድላሉ፤ የቀሩትንም ያሳድዳሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የእግዚአብሔር ጥበቡ እንዲህ አለች፦ እነሆ፥ እኔ ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ይገድላሉ፤ ያሳድዳሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ደግሞ የእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ አለች፦ ወደ እርሱ ነቢያትንና ሐዋርያትን እልካለሁ፥ ከእነርሱም ይገድላሉ ያሳድዱማል፥ |
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳና በሰማርያ ሁሉ፣ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነሣ፤ ከቤት ወደ ቤት በመግባትም ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ እያወጣ ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር።
አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ አንዳንዶቹ ነቢያት፣ አንዳንዶቹም ወንጌል ሰባኪዎች፣ ሌሎቹ ደግሞ እረኞችና አስተማሪዎች ይሆኑ ዘንድ የሰጠ እርሱ ነው፤
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”