“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ውጫቸው በኖራ ተለስነው የሚያምሩ፣ ውስጣቸው ግን በሙታን ዐፅምና በብዙ ርኩሰት የተሞላ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!
ሉቃስ 11:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አባቶቻችሁ የገደሏቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምታበጃጁ፣ ወዮላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ወዮላችሁ!አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብሮች ትሠራላችሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም አባቶቻችሁ ለገደሉአቸው ነቢያት መቃብሮቻቸውን በማስጌጥ የምትሠሩ ስለ ሆናችሁ ወዮላችሁ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ትሠራላችሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቶቻችሁ የገደሉአቸውን የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፥ ወዮላችሁ። |
“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ውጫቸው በኖራ ተለስነው የሚያምሩ፣ ውስጣቸው ግን በሙታን ዐፅምና በብዙ ርኩሰት የተሞላ መቃብሮችን ስለምትመስሉ ወዮላችሁ!