ሉቃስ 11:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሕዝብ እየተሰበሰበ በሄደ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ታምራዊ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝብም በብዛት እየተሰበሰቡ በነበሩ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትን ይፈልጋል፤ ከዮናስም ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጥተው በተሰበሰቡ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክት ለማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው ሳሉ እንዲህ ይላቸው ጀመረ ፥ “ይቺ ትውልድ ክፉ ናት፤ ምልክትም ትሻለች፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጣትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ምልክት ይፈልጋል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። |
ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የእፉኝት ልጆች! ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ?
በዚህ ዘማዊና ኀጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፣ የሰው ልጅም በአባቱ ግርማ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋራ ሲመጣ ያፍርበታል።”
በዚያ ጊዜ፣ በብዙ ሺሕ የሚቈጠር ሕዝብ እርስ በርስ እስኪረጋገጥ ድረስ ተሰብስቦ ሳለ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፤ “ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ ይህም ግብዝነት ነው።
ኢየሱስም “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጅህን ወደዚህ አምጣው!” አለ።
እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለመፈጸም ትሻላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ በርሱ ዘንድ እውነት ስለሌለ በእውነት አልጸናም፤ እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት በመሆኑ ሐሰትን ሲናገር፣ የሚናገረው ከራሱ አፍልቆ ነው፤