ኤልሳዕ ወደ ጌልገላ ተመለሰ፤ በዚያም አገር ራብ ነበረ። የነቢያት ማኅበር በፊቱ ተቀምጠው ሳለ አገልጋዩን፣ “ትልቁን ምንቸት ጣድና ለእነዚህ ሰዎች ወጥ ሥራላቸው” አለው።
ሉቃስ 10:39 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም ማርያም የተባለች እኅት ነበረቻት፤ ማርያምም ቃሉን እየሰማች በጌታ እግር ሥር ተቀምጣ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሷም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ እርሷም ደግሞ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ቃሉን ትሰማ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፤ ይህች ማርያም በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ትምህርቱን ታደምጥ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያም የምትባል እኅትም ነበረቻት፤ እርስዋም ከጌታችን ኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ትምህርቱን ትሰማ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእርስዋም ማርያም የምትባል እኅት ነበረቻት፥ እርስዋም ደግሞ ቃሉን ልትሰማ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ነበረች። |
ኤልሳዕ ወደ ጌልገላ ተመለሰ፤ በዚያም አገር ራብ ነበረ። የነቢያት ማኅበር በፊቱ ተቀምጠው ሳለ አገልጋዩን፣ “ትልቁን ምንቸት ጣድና ለእነዚህ ሰዎች ወጥ ሥራላቸው” አለው።
ሕዝቡም የተደረገውን ነገር ለማየት ከያሉበት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ። አጋንንት የወጡለትም ሰው ልብስ ለብሶ፣ ወደ ልቡናው ተመልሶ፣ በኢየሱስም እግር ሥር ተቀምጦ ባዩት ጊዜ ፈሩ።
ማርያምም ዋጋው ውድ የሆነ፣ ግማሽ ሊትር ንጹሕ የናርዶስ ሽቱ አምጥታ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ እግሮቹንም በጠጕሯ አበሰች፤ ቤቱንም የሽቱው መዐዛ ሞላው።
“እኔ በኪልቅያ በምትገኘው በጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ስሆን፣ ያደግሁት ግን በዚህ ከተማ ነው። የአባቶቻችንን ሕግ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ በሚገባ ተምሬአለሁ፤ ዛሬ እናንተ እንዲህ የምትቀኑለትን ያህል እኔም ለእግዚአብሔር እቀና ነበር።