ሰቈቃወ 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ቀኑን ሁሉ በመደጋገም፣ እጁን በላዬ ላይ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀኑን ሙሉ እኔን ብቻ መላልሶ ቀጣኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘወትር ቀኑን ሁሉ እጁን በላዬ መለሰ። |
የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዷል፤ እጁን አንሥቶ መትቷቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
እግዚአብሔር ለዚያ ሰው ፈጽሞ ይቅርታ አያደርግለትም፤ ቍጣውና ቅናቱ በርሱ ላይ ይነድድበታል። በዚህ መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።