ሰቈቃወ 3:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፊቱ አስወጣኝ፤ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ብርሃን ወደሌለበት ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃን ወደሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርሃን ወደ ሌለበት ወደ ጨለማ መርቶ ወሰደኝ። |
ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይመጣም፤ ብርሃንን ፈለግን፤ ነገር ግን ሁሉ ጨለማ ነው፤ የብርሃንን ጸዳል ፈለግን፤ የምንሄደው ግን በድንግዝግዝታ ነው።
ጨለማን ሳያመጣ፣ በሚጨልሙትም ተራሮች ላይ፣ እግሮቻችሁ ሳይሰናከሉ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ። ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ፤ እርሱ ወደ ጨለማ ይለውጠዋል፤ ድቅድቅ ጨለማም ያደርገዋል።
ጌታ የጽዮንን ሴት ልጅ፣ በቍጣው ደመና እንዴት ጋረዳት! ከሰማይ ወደ ምድር፣ የእስራኤልን ክብር ወርውሮ ጣለው፤ በቍጣው ቀን፣ የእግሩን መቀመጫ አላስታወሰም።
በእኩለ ቀን፣ በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። በየዕለቱ ትጨቈናለህ፤ ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።
የሥልጣን ስፍራቸውን ያልጠበቁትን፣ ነገር ግን መኖሪያቸውን የተዉትን መላእክት በዘላለም እስራት እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ በጨለማ ጕድጓድ ጠብቋቸዋል።