ኢያሱ 4:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱም ከዮርዳኖስ ወንዝ ያወጧቸውን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች በጌልገላ ተከላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አኖራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌልገላም ኢያሱ ከዮርዳኖስ ወንዝ የተወሰዱትን ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አቁሞ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ከዮርዳኖስ ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች በጌልገላ አቆማቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮርዳኖስም ውስጥ የወሰዱአቸውን እነዚያን አሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ኢያሱ በጌልገላ አቆማቸው። |
እንዲሁም ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ልክ ካህናቱ ከቆሙበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ አንሥተው በመሸከም ከእናንተ ጋራ እንዲሻገሩና ዛሬ በምታድሩበት ቦታ እንዲያኖሯቸው ንገራቸው።”
እስራኤላውያንም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረውም መሠረት፣ በእስራኤል ነገዶች ቍጥር ልክ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል አነሡ፤ ወደ ሰፈራቸውም ይዘው በመሻገር በዚያ አኖሯቸው።