ኢያሱ 23:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለመውደድ ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን አምላካችሁንም የምትወድዱ መሆናችሁን እጅግ በጥንቃቄ አስተውሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ አምላካችሁን እግዚአብሔርን የምትወዱ መሆን እንደሚገባችሁ በጥንቃቄ አስቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላካችን እግዚአብሔርን ትወድዱት ዘንድ ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱት ዘንድ ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ። |
“እንግዲህ በገደብ የለሽ ሕይወት፣ በመጠጥ ብዛትና ስለ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝልና ያ ቀን እንደ ወጥመድ ድንገት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤
አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ በመንገዱም እንድትሄድና ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን እንድትጠብቅ አዝዝሃለሁ፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል።
ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከርሱ ጋራ እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወትህ ነው፤ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረዥም ዕድሜ ይሰጥሃል።
ዐይኖቻችሁ ያዩአቸውን ነገሮች እንዳትረሱ፣ ደግሞም በሕይወት እስካላችሁ ድረስ ከልባችሁ እንዳይጠፉ ብቻ ተጠንቀቁ፣ ነቅታችሁም ራሳችሁን ጠብቁ። እነዚህን ለልጆቻችሁና ከእነርሱ በኋላ ለሚወለዱት ልጆቻቸው አስተምሯቸው።
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ፣ አምላካችሁን እግዚአብሔርን እንድትወድዱ፣ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄዱ፣ ትእዛዙን እንድትፈጽሙ፣ እርሱንም አጥብቃችሁ እንድትይዙት እንዲሁም በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁ እንድታገለግሉት የሰጣችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ነቅታችሁ ጠብቁ።”