ኢያሱ 22:34 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሮቤልና የጋድ ወገኖችም፣ እግዚአብሔር አምላክ ለመሆኑ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው፤ በማለት መሠዊያውን “ምስክር” ብለው ጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ “ጌታ አምላክ እንደሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው” ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም መሠዊያውን “የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ ምስክር” ብሎ ጠራው። እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆነ ይህ በመካከላቸው ምስክር ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆችም፦ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆነ ይህ በመካከላችን ምስክር ነው ሲሉ መሠዊያውን ምስክር ብለው ጠሩት። |
ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያዩ፣ በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አምላክ እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ ነው! እግዚአብሔር እርሱ እውነተኛ አምላክ ነው!” አሉ።
“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደ ሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።
በሌላም በኩል የሚቃጠል መሥዋዕታችንን፣ ሌላውን ቍርባናችንንና የኅብረት መሥዋዕታችንን ይዘን በተቀደሰው ስፍራ እግዚአብሔርን እንደምናመልክ መሠዊያው በእኛና በእናንተ እንዲሁም በሚቀጥሉት ትውልዶች መካከል ምስክር ይሆናል። ስለዚህ ወደ ፊት ዘሮቻችሁ ዘሮቻችንን፣ ‘ከእግዚአብሔር ዘንድ ድርሻ የላችሁም’ ሊሏቸው አይችሉም።
ኢያሱም ሕዝቡን ሁሉ፣ “እነሆ፤ ይህ ድንጋይ፣ እግዚአብሔር የተናገረንን ሁሉ ሰምቷል፣ በእኛም ይመሰክርብናል፤ እናንተም በአምላካችሁ ዘንድ እውነተኞች ሆናችሁ ባትገኙ ምስክር ይሆንባችኋል” አላቸው።