ኢያሱ 2:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ የምናደርገውን ብትናገሪ ግን፣ ካስማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን ነገራችንን ግን ብትናገሪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ነጻ እንሆናለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገውን ነገር ለማንም ነግረሽ ብትገኚ፥ በጥያቄሽ መሠረት የገባንልሽን ቃል ለመጠበቅ አንገደድም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይህን ነገራችንን ብትገልጪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሓን እንሆናለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንን ነገራችንን ግን ብትገልጪ ከዚህ ካማልሽን መሐላ ንጹሐን እንሆናለን። |
ማንም ከቤትሽ ወጥቶ መንገድ ላይ ቢገኝ፣ ደሙ በራሱ ላይ ነው፤ እኛ አንጠየቅበትም፤ ነገር ግን ከአንቺ ጋራ ቤት ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው ከተነካ የደሙ ባለዕዳ እኛ እንሆናለን።
እርሷም፣ “ይሁን፤ ባላችሁት ተስማምቻለሁ” ስትል መለሰች። ከዚያም ሰደደቻቸው፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀይ ፈትሉንም በመስኮቷ ላይ አንጠለጠለችው።