ኢያሱ 2:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “የሚከታተሏችሁ ሰዎች እንዳያገኟችሁ ወደ ኰረብቶቹ ሂዱ፤ እነርሱ እስኪመለሱም ድረስ ሦስት ቀን በዚያ ተሸሸጉ፤ ከዚያ በኋላ መንገዳችሁን ትቀጥላላችሁ” አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም እንዲህ አለቻቸው፦ “አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ ከዚያም በኋላ መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ስትል መከረቻቸው፤ “ወደ ኮረብታማው አገር ሂዱ፤ ይህ ካልሆነ ግን የንጉሡ መልእክተኞች ሊያገኙአችሁ ይችላሉ፤ በዚያም እነርሱ እስኪመለሱ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ተደብቃችሁ ቈዩ፤ ከዚያን በኋላ ጒዞአችሁን መቀጠል ትችላላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም፥ “የሚከተሉአችሁ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ የሚከተሉአችሁም እስከሚመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ በኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አሳዳጆቹ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፥ አሳዳጆቹም እስኪመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፥ ኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ አለቻቸው። |
እነርሱም ወጥተው ወደ ኰረብቶቹ ሄዱ፤ የሚከታተሏቸውም ሰዎች በየመንገዱ ሁሉ ላይ ፈልገውና ዐጥተው እስኪመለሱ ድረስ፣ ሦስት ቀን በዚያው ተሸሸጉ።
ዳዊት በምድረ በዳ ባሉ ምሽጎችና በዚፍ ምድረ በዳ ኰረብቶች ተቀመጠ፤ ሳኦልም በየዕለቱ ይከታተለው ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊትን አሳልፎ አልሰጠውም።