ኢያሱ 18:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለብንያም ነገድ የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ። በዕጣ የደረሳቸውም ምድር የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች ርስት መካከል ሲሆን እንደሚከተለው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የዕጣቸውም ግዛት በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የብንያም ነገድ የርስት ድርሻ በየወገናቸው ወጣ፤ ለእነርሱም የተመደበላቸው ርስት የሚገኘው በይሁዳና በዮሴፍ ነገዶች መካከል ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምም ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው በቅድሚያ ወጣ፤ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምም ልጆች ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ። |
በሰሜን ያለው ድንበራቸው ከዮርዳኖስ ይነሣና የኢያሪኮን ሰሜናዊ ተረተር ዐልፎ፣ በስተ ምዕራብ ወዳለው ኰረብታማ ምድር በማምራት፣ እስከ ቤትአዌን ምድረ በዳ ይዘልቃል።