ዮሐንስ 7:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕጋችን፣ አስቀድሞ አንድን ሰው ሳይሰማና ምን እንዳደረገ ሳይረዳ ይፈርድበታልን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፥ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሕጋችን መሠረት አንድ ሰው የክስ መልስ አስቀድሞ ሳይሰማለትና ምን እንዳደረገ ሳይታወቅ ይፈረድበታልን?” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ፤ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ማንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አላቸው። |
“ ‘ሰው የገደለ ማንኛውም ሰው በሞት የሚቀጣው ምስክሮች ሲመሰክሩበት ብቻ ነው፤ ይሁን እንጂ ማንም ሰው በአንድ ምስክር ብቻ በሞት አይቀጣም።
ጳውሎስም፣ “አንተ በኖራ የተለሰንህ ግድግዳ! እግዚአብሔር ደግሞ አንተን ይመታሃል፤ በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለህ፣ ያለ ሕግ ስላስመታኸኝ አንተ ራስህ ሕጉን ጥሰሃል” አለው።
በፍርድ አድልዎ አታድርጉ፤ ትልቁንም ትንሹንም እኩል እዩ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንኛውንም ሰው አትፍሩ። ከዐቅማችሁ በላይ የሆነውን ሁሉ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔ አየዋለሁ።”