ዮሐንስ 7:47 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያንም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተም ተታልላችኋል ማለት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳውያንም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፤ “እናንተ ደግሞ ሳታችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሪሳውያን ግን እንዲህ አሉ፦ “እናንተም ደግሞ ተሳሳታችሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያንም መልሰው እንዲህ አሉአቸው፥ “እናንተም ደግሞ ተሳሳታችሁን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ፈሪሳውያን፦ “እናንተ ደግሞ ሳታችሁን? |
ይኸውም የእናንተኑ ወደምትመስለው ምድር እህልና የወይን ጠጅ፣ ዳቦና የወይን ተክል፣ የወይራ ዛፍና ማር ወዳለባት እስካገባችሁ ድረስ ነው፤ እናንተም ሞትን ሳይሆን ሕይወትን ምረጡ።’ “ሕዝቅያስ፣ ‘እግዚአብሔር ይታደገናል’ በማለት ስለሚያሳስታችሁ አትስሙት።
አሁንም ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!”