ዮሐንስ 5:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “ያ የፈወሰኝ ሰው፣ ‘መተኛህን ተሸክመህ ሂድ’ ብሎኛል” ሲል መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን “ያዳነኝ ያ ሰው ‘አልጋህን ተሸክመህ ሂድ፤’ አለኝ፤” ብሎ መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን “ያዳነኝ ሰው አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” ብሎኛል አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም መልሶ፥ “ያዳነኝ እርሱ፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ ያዳነኝ ያ ሰው፦ አልጋህን ተሸክመህ ሂድ አለኝ ብሎ መለሰላቸው። |
ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፣ “ኀጢአተኛ፣ እንዲህ ያሉትን ታምራዊ ምልክቶች እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም አለመስማማት ተፈጠረ።