በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።
ኢዩኤል 3:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳ ለዘላለም፣ ኢየሩሳሌምም ለትውልድ ሁሉ መኖሪያ ትሆናለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ይሁዳ ለዘለዓለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እስከ አሁን ድረስ ሳልበቀልላቸው የቀረሁትን የንጹሐንን ደም እበቀላለሁ፤ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ግን ለዘለዓለም ለሕዝቤ መኖሪያ ይሆናሉ፤ እኔም እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ላይ እኖራለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይሁዳ ለዘለዓለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ይሁዳ ለዘላለም፥ ኢየሩሳሌምም ለልጅ ልጅ መኖሪያ ይሆናል። |
በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ።
አባቶቻችሁ በኖሩበት፣ ለባሪያዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት ምድር ይኖራሉ። በዚያም እነርሱ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው ለዘላለም ይኖራሉ፤ ባሪያዬ ዳዊትም ለዘላለም ንጉሣቸው ይሆናል።