ኢዩኤል 3:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቧልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ በፍርድ ሸለቆ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ደርሶአል፤ ስለዚህ ቊጥሩ እጅግ የበዛ ሕዝብ በዚያ ተሰብስቦአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና ውካታዎች በፍርድ ሸለቆ ተሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ። |
በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ በመንግሥታትም መካከል፣ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሰራዊቱን ለጦርነት አሰልፏል።
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱ ተራራዬም የማስጠንቀቂያውን ድምፅ አሰሙ። በምድሪቱ የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና፤ እርሱም በደጅ ነው።
በሰራዊቱ ፊት፣ እግዚአብሔር ያንጐደጕዳል፤ የሰራዊቱ ብዛት ስፍር ቍጥር የለውም፤ ትእዛዙንም የሚያደርግ እርሱ ኀያል ነው፤ የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ፣ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ ማንስ ሊቋቋመው ይችላል?
አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፤ ወደ ኢዮሣፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ ስለ ርስቴ፣ ስለ ሕዝቤ፣ ስለ እስራኤል፣ በዚያ ልፈርድባቸው እገባለሁ፤ ምድሬን ከፋፍለዋል፤ ሕዝቤንም በሕዝቦች መካከል በታትነዋልና።
“ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው፤ ቅርብ ነው ፈጥኖም ይመጣል፤ በእግዚአብሔር ቀን የሚሰማው ልቅሶ መራራ ነው፤ በዚያ ጦረኛውም ምርር ብሎ ይጮኻል፤