ኢዩኤል 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነርሱ ፊት ሕዝቦች ይርዳሉ፤ የሁሉም ፊት ይገረጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቁራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱን በሚያዩበት ጊዜ ሕዝቦች ይርበደበዳሉ፤ የሰውም ሁሉ ፊት በፍርሃት ይገረጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፤ የሰውም ፊት ሁሉ እንደ ድስት ጥላሸት ይጠቍራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፊታቸው አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፥ የሰውም ፊት ሁሉ ይጠቍራል። |
ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።
እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?