ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ።
ኢዩኤል 2:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንቆችን በሰማያት፣ እንዲሁም በምድር፣ ደምና እሳት፣ የጢስም ዐምድ አሳያለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሰማይና በምድር፥ ድንቅ ነገሮችን አሳያለሁ፤ ደምና እሳት፥ የጢስ ዐምድም ይታያል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፤ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይ በሰማይ ድንቆችን አሳያለሁ፥ በታች በምድርም ደምና እሳት የጢስም ጭጋግ። |
ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ።
ከከርቤና ከዕጣን፣ ከነጋዴም ቅመማ ቅመም ሁሉ በተዘጋጀ ሽቱ፣ መዐዛዋ የሚያውድ፣ እንደ ጢስ ዐምድ ከምድረ በዳ የምትወጣው ይህች ማን ናት?
“ወዲያውኑ ከእነዚያ ከመከራው ቀናት በኋላ፣ “ ‘ፀሓይ ትጨልማለች፤ ጨረቃ ብርሃኗን ትከለክላለች፤ ከዋክብት ከሰማይ ይረግፋሉ፤ የሰማይ ኀይላትም ይናጋሉ።’
የጋይ ሰዎች ወደ ኋላ ዞረው ሲመለከቱ የከተማዪቱ ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ አዩ፤ ወደ ምድረ በዳ ይሸሹ የነበሩት እስራኤላውያን ፊታቸውን ስላዞሩባቸውም፣ በየትኛውም በኩል ማምለጫ መንገድ አልነበራቸውም።
የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ወደ ምድር ተጣለ፤ የምድር አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለመውም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።