ሥርዐቱንና ከአባቶቻቸው ጋራ የገባውን ኪዳን፣ ለእነርሱም የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ናቁ፤ ከንቱ ጣዖታትን ተከትለው ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ፤ እግዚአብሔር፣ “እነርሱ የሚያደርጉትን እንዳታደርጉ” ብሎ ቢያዝዛቸው እንኳ በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ፤ እግዚአብሔር እንዳያደርጉ የከለከላቸውንም ፈጸሙ እንጂ አልተዉም።
ኤርምያስ 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፣ ከንቱ ነገርን የተከተሉት፣ ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት፣ ምን ጥፋት አግኝተውብኝ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፦ “አባቶቻችሁ ከእኔ የራቁት፥ ከንቱነትንም የተከተሉት፥ ከንቱም የሆኑት ምን ስሕተት አግኝተውብኝ ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኔ ርቀው የሄዱት በኔ ላይ ምን ጥፋት አግኝተው ነው? እነርሱም ከንቱ የሆኑትን ጣዖቶች በማምለካቸው ራሳቸውን ከንቱዎች አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አባቶቻችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከንቱነትንም የተከተሉ፥ ከንቱም የሆኑ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው? |
ሥርዐቱንና ከአባቶቻቸው ጋራ የገባውን ኪዳን፣ ለእነርሱም የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ናቁ፤ ከንቱ ጣዖታትን ተከትለው ራሳቸውም ከንቱ ሆኑ፤ እግዚአብሔር፣ “እነርሱ የሚያደርጉትን እንዳታደርጉ” ብሎ ቢያዝዛቸው እንኳ በዙሪያቸው ያሉትን አሕዛብ ተከተሉ፤ እግዚአብሔር እንዳያደርጉ የከለከላቸውንም ፈጸሙ እንጂ አልተዉም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።
ከአሕዛብ ከንቱ ጣዖቶች መካከል ዝናብ ሊያዘንብ የሚችል አለን? ሰማያትስ በራሳቸው ማካፋት ይችላሉን? አይ! አይችሉም፣ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ነህ፣ ስለዚህም ተስፋችን በአንተ ላይ ነው።
“የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤ “እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤ፣ ‘እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?
እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ ከሩቅ ምድር ስማ፤ “እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ንጉሧስ በዚያ አይኖርምን?” “በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣ እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”
“የሰው ልጅ ሆይ፤ ወንድሞችህ፣ የራስህ ዘመዶችና የእስራኤል ቤት ሁሉ፤ ‘ከእግዚአብሔር ርቀዋል፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታናለች’ ብለው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የተናገሩባቸው ናቸው።
“እናንተ ሰዎች፤ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እኮ እንደ እናንተው ሰዎች ነን። እናንተም ደግሞ ከነዚህ ከንቱ ነገሮች ርቃችሁ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ ወንጌልን እንሰብክላችኋለን።
እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።