ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ።
ኤርምያስ 2:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የታመንሽባቸውን እግዚአብሔር ስላዋረደ፣ በእነርሱም ስለማይከናወንልሽ፣ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያም ትወጫለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ ደግሞ እጆችሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ትወጫለሽ፥ ምክንያቱም ጌታ የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ በዕፍረት ከዚያ ቦታ ትሄጂአለሽ፤ እኔ እግዚአብሔር አንቺ የምትታመኝባቸውን ሁሉ ስላስወገድኩ ከእነርሱ የምታገኚው ምንም ነገር አይኖርም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ተስፋሽን አስቈርጦሻልና፥ በእርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። |
ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ።
እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ መሪያችንም እርሱ ነው። መለከት የያዙ ካህናቱም የጦርነቱን ድምፅ በእናንተ ላይ ያሰማሉ። እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፤ አይቀናችሁምና፣ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋራ አትዋጉ።”
ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
ከሞት ጋራ የገባችሁት ቃል ኪዳን ይሻራል፤ ከሲኦልም ጋራ ያደረጋችሁት ስምምነት ይፈርሳል፤ ታላቁ መቅሠፍት እየጠራረገ ሲያልፍ፣ እናንተም ትጠራረጋላችሁ።
መሳፍንት አገልጋዮቻቸውን ውሃ ፍለጋ ይሰዳሉ፤ እነርሱ ወደ ውሃ ጕድጓዶች ይወርዳሉ፤ ነገር ግን ውሃ አያገኙም፤ ዐፍረውና ተስፋ ቈርጠው፣ ራሳቸውን ተከናንበው፣ ባዶ እንስራ ይዘው ይመለሳሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”
ሴዴቅያስንም ወደ ባቢሎን ይወስደዋል፤ በፍርዴ እስከምጐበኘውም ድረስ በዚያ ይቈያል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ከባቢሎናውያን ጋራ ብትዋጉ አይሳካላችሁም” ይላል’ ትላለህ።”