ኤርምያስ 2:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ ለምን ትሮጫለሽ? አሦር እንዳዋረደሽ፣ ግብጽም እንዲሁ ያዋርድሻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገድሽን እጥፍ ታደርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? በአሦር እንዳፈርሽ በግብፅም ታፍሪያለሽ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገድሽን ትለውጪ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል። |
“ ‘አልረከስሁም፣ በኣሊምን አልተከተልሁም’ እንዴት ትያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ምን እንዳደረግሽ እስኪ አስቢ፣ ምንስ እንደ ፈጸምሽ ተገንዘቢ፤ እንደምትፋንን ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ይፈጥራል፤ ሴት በወንድ ላይ ከበባ ታደርጋለች።”
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ትጠይቁኝ ዘንድ ወደ እኔ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ ‘ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሰራዊት ወደ ገዛ አገሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል፤
ኤፍሬም የነፋስ እረኛ ነው፤ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛል። ከአሦር ጋራ ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ የወይራ ዘይትንም ወደ ግብጽ ይልካል።
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”
“ኤፍሬም ሕመሙን፣ ይሁዳም ቍስሉን ባየ ጊዜ፣ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ ቍስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።