ኤርምያስ 2:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድረ በዳ እንደ ለመደች፣ በፍትወቷ ነፋስን እንደምታነፈንፍ፣ የሜዳ አህያ ነሽ፤ ከመጐምጀቷ ማን ሊገታት ይችላል? ለሚፈልጓት ሁሉ ያለ ምንም ድካም በፍትወቷ ወራት በቀላሉ ትገኝላቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፤ ከጋለው ምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በበረሓ መኖርን የለመደች የሜዳ አህያ፥ ፍትወት በተቀሰቀሰባት ጊዜ ማን ሊቈጣጠራት ይችላል? ወንዶች የሜዳ አህዮች ያሉበትን ስፍራ፥ ራስዋ አነፍንፋ ስለምትደርስበት፥ እነርሱ እርስዋን በመፈለግ መድከም አያስፈልጋቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድረ በዳ ባሉ ውኃዎች ተዘረጋች፤ በሰውነቷም ምኞት ትወሰዳለች፤ ይይዟታል፤ የሚመልሳት ግን የለም፤ የሚሹአትም አይደክሙም፤ በተዋረደችበትም ጊዜ ያገኙአታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምኞትዋ ነፋስን እንደምታሸትት፥ በምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ፥ ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚሹአት ሁሉ አይደክሙም፥ በወራትዋ ያገኙአታል። |
ዛፉን፣ ‘አንተ አባቴ ነህ’ ድንጋዩንም፣ ‘አንተ ወለድኸኝ’ አሉ፤ ፊታቸውን ሳይሆን፣ ጀርባቸውን ሰጥተውኛልና፤ በመከራቸው ጊዜ ግን፣ ‘መጥተህ አድነን’ ይላሉ።
ማንኛዋም አመንዝራ ሴት ዋጋ ይከፈላታል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ስጦታ ታበረክቻለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋራ ያመነዝሩ ዘንድ እጅ መንሻ ታቀርቢላቸዋለሽ።