ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ።
ኤርምያስ 2:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልዩ ቅጠል ብትታጠቢ፣ ብዙ ሳሙና ብትጠቀሚም፣ የበደልሽ ዕድፍ አሁንም በፊቴ ነው፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙናን አብዝተሽ ብትጠቀሚ እንኳ፥ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቱንም ያኽል በእንዶድና በብዙ ሳሙና ብትታጠቢ፥ በደልሽ ግልጥ ሆኖ ይታየኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙና ብታበዢ፥ በእኔ ፊት በኀጢአትሽ ረክሰሻል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእንዶድ ብትታጠቢም፥ ለራስሽም ሳሙና ብታበዢ፥ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
ከዚያም ዳዊት፣ “እንግዲያውስ ዛሬ እዚህ ዕደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው። ስለዚህ ኦርዮን በዚያ ዕለትና በማግስቱም እዚያው ኢየሩሳሌም ቈየ።
“ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ለዛገችው ብረት ድስት ዝገቷም ለማይለቅ፣ ደም ላፈሰሰችው ከተማ ወዮላት! መለያ ዕጣ ሳትጥል አንድ በአንድ አውጥተህ ባዶ አድርገው።