በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።
ኤርምያስ 12:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳ ተነሥታብኛለች፤ በእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ ስለዚህ ጠላኋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን በእኔ ላይ አንሥታለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ በእኔ ላይ ተነሥተው እንደ ዱር አንበሳ ያገሡብኛል፤ ይህንንም አድራጎታቸውን እጠላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስቴ በዱር እንደ አለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋንም አንሥታብኛለች፤ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴ በዱር እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፥ ድምፅዋን አንሥታብኛለች፥ ስለዚህ ጠልቻታለሁ። |
በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።
“በጌልገላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሣ፣ እኔ በዚያ ጠላኋቸው፤ ስለ ሠሩት ኀጢአት፣ ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህም አልወድዳቸውም፤ መሪዎቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸው።
ጌታ እግዚአብሔር “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፤ ምሽጎቹንም ጠልቻለሁ፤ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ፣ አሳልፌ እሰጣለሁ” ሲል በራሱ ምሏል፤ ይላል የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር።