ያዕቆብ 2:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ፤ እርሱም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የተባለው ቃል ተፈጸመ፤ በዚህ ሁኔታ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጽሐፍም “አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት፤” ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ። |
አምላካችን ሆይ፤ የዚህችን ምድር ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ያስወጣህና ለወዳጅህ ለአብርሃም ዘሮች ለዘላለም የሰጠሃቸው አንተ አይደለህምን?
ሰው ከባልንጀራው ጋራ እንደሚነጋገር እግዚአብሔር ከሙሴ ጋራ ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር፤ ከዚያም ሙሴ ወደ ሰፈሩ ይመለሳል፤ ረዳቱ የነበረው ብላቴናው የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፣ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፉ ቃል መፈጸም ስላለበት፣
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። ኤልያስ በእስራኤል ላይ ክስ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንዳቀረበ፣ መጽሐፍ ስለ እርሱ ምን እንደሚል አታውቁምን?
መጽሐፍ ግን ዓለም ሁሉ የኀጢአት እስረኛ መሆኑን ያውጃል፤ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው ተስፋ ለሚያምኑት ሁሉ ይሰጥ ዘንድ ነው።
ምክንያቱም በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “እነሆ፤ የተመረጠና የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አኖራለሁ፤ በርሱም የሚያምን ፈጽሞ አያፍርም።”