“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።
ሆሴዕ 3:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ከእኔ ጋራ ብዙ ቀን ተቀመጪ፤ አታመንዝሪ ወይም ሌላ ሰው አትውደጂ፤ እኔም ከአንቺ ጋራ እኖራለሁ” ብዬ ነገርኋት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእርሷም፦ “የእኔ ሆነሽ ለብዙ ወራት ተቀመጪ፥ አታመንዝሪም፥ ለሌላ ሰውም አትሁኚ፤ እኔም እንዲሁ እሆንልሻለሁ” አልኋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሳታመነዝሪና ሰውነትሽን ለማንኛውም ወንድ ሳትሰጪ እኔን እየጠበቅሽ ለብዙ ጊዜ መቈየት አለብሽ፤ እኔም ለአንቺ እንዲሁ አደርግልሻለሁ” ብዬ ነገርኳት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፤ አታመንዝሪም፤ ሌላ ሰውንም አታግቢ፤ እኔም ከአንቺ ጋር እኖራለሁ” አልኋት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእኔ ጋር ብዙ ወራት ተቀመጪ፥ አታመንዝሪም፥ ለሌላ ሰውም አትሁኚ፥ እኔም እንዲሁ እሆንልሻለሁ አልኋት። |
“በምድሪቱ ከሚኖሩት ጋራ ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና መሥዋዕትም ባቀረቡላቸው ጊዜ ይጋብዙሃል፤ አንተም መሥዋዕታቸውን ትበላለህ።
ስትማረክ የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፤ እቤትህ ተቀምጣ ለአባትና ለእናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፣ ልትደርስባትና ባል ልትሆናት፣ እርሷም ሚስት ልትሆንህ ትችላለች።