ሐጌ 1:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እስኪ መንገዳችሁን ልብ በሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያላችሁበትን ሁኔታ አስቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ። |
ሰውየውም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በዐይንህ እይ፤ በጆሮህ ስማ፤ የማሳይህንም ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፤ ወደዚህ የመጣኸው ለዚህ ነውና ያየኸውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”
ደግሞም እንዲህ አለኝ፤ “ዳንኤል ሆይ፤ አትፍራ፤ ማስተዋልን ለማግኘትና በአምላክህም ፊት ራስህን ለማዋረድ ከወሰንህበት ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ ቃልህ ተሰምቷል፤ እኔም የቃልህን መልስ ይዤ መጥቻለሁ።
ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?