እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው።
ዘፍጥረት 6:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወፍ እንደ ወገኑ፥ ከእንስሳም እንደ ወገኑ፥ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንደ ወገኑ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወፎች ሁሉ በየወገናቸው፥ ከእንስሳም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ ከሚሳቡ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በየወገናቸው ከአንተ ጋር ይመገቡ ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። |
እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው።
እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ።