ዘፍጥረት 41:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ ፈርዖን ዮሴፍን “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ! አሁን በመላው የግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ አድርጌሃለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዮሴፍን፦ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ አለው። |
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ፣ እግዚአብሔር የግብጻዊውን ቤት ባረከ፤ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
ከዚህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላዪቱ ግብጽ ያላንተ ትእዛዝ እጁንም ሆነ እግሩን ልውስ የሚያደርግ አይኖርም” አለው።
በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዥ ነበር፤ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደ ደረሱ፣ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው እጅ ነሡት።
“ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፣ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብጽ ምድር ላይ ገዥ አደረገኝ።
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ከንጉሡ ከጠረክሲስ ቀጥሎ ሁለተኛ፣ ከአይሁድ መካከልም ቀዳሚውን ስፍራ የያዘ ሰው ነበር፤ ለወገኖቹ መልካም በማድረጉና ለአይሁድም ሁሉ ደኅንነት የቆመ በመሆኑ፣ በብዙዎቹ አይሁድ ወገኖቹ ዘንድ እጅግ የተከበረ ነበር።
ንጉሡም ዳንኤልን በከፍተኛ ሥልጣን ላይ አስቀመጠው፤ እጅግ ብዙ ስጦታዎችንም ሰጠው፤ የመላው ባቢሎን አውራጃ ገዥ አደረገው፤ በባቢሎን ጠቢባን ሁሉ ላይም አለቃ አድርጎ ሾመው።
ከመሳፍንቱና ከበላይ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ ይልቅ ዳንኤል ልዩ የጥበብ መንፈስ የሞላበት ሆኖ በመገኘቱ፣ ንጉሡ በመላው ግዛቱ ላይ ሊሾመው ዐሰበ።
ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽም ንጉሥ በፈርዖን ፊት ሞገስና ጥበብን አጐናጸፈው፤ ፈርዖንም በግብጽና በቤተ መንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።