ዘፍጥረት 41:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕቅዱንም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕቅዱም ለፈርዖንና ለባለሟሎቹ ሁሉ መልካም ሆኖ ታያቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩም ፈርዖንንና ሰዎቹን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩም በፈርዖንና በሎሌዎቹ ፊት መልካም ሆነ፤ |
አክዓብም ናቡቴን፣ “የወይን ተክል ቦታህ ከቤተ መንግሥቴ አጠገብ ስለ ሆነ፣ የአትክልት ቦታ እንዳደርገው ልቀቅልኝ፤ በምትኩ ከዚህ የበለጠ የወይን ተክል ቦታ እሰጥሃለሁ፤ የተሻለ ሆኖ ከታየህም የሚያወጣውን ገንዘብ እከፍልሃለሁ” አለው።
ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽም ንጉሥ በፈርዖን ፊት ሞገስና ጥበብን አጐናጸፈው፤ ፈርዖንም በግብጽና በቤተ መንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሾመው።
ካህኑ ፊንሐስና የእስራኤላውያን የጐሣ መሪዎች የነበሩት የማኅበረ ሰቡ አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ወገኖች ያሉትን በሰሙ ጊዜ ተደሰቱ።