ዘፍጥረት 41:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አስቀድሜ ለፈርዖን እንደ ተናገርሁት፣ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርኩት፥ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልክ እንደ ነገርኩህ ነው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ነገር አስቀድሞ ገልጦልሃል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለፈርዖን የነገርሁት ነገር ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳየው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለፈርዖን የነገርሁት ነገር ይህ ነው እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳየው። |
ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዐይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።
ሕልሙ ለፈርዖን በሁለት መልክ በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለ ሆነ ነው፤ ይህንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል።
የሰው እጅ ሳይነካው ከተራራ ተፈንቅሎ የወረደውና ብረቱን፣ ናሱን፣ ሸክላውን፣ ብሩንና ወርቁን ያደቀቀው ድንጋይ ራእይ ትርጓሜ ይህ ነው፤ “ታላቁ አምላክ ወደ ፊት የሚሆነውን ለንጉሡ አሳይቶታል፤ ሕልሙ እውነት ነው፤ ትርጓሜውም የታመነ ነው።”