ዘፍጥረት 41:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፣ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፥ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሁለት ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሕልም አየ፤ እርሱ በሕልሙ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁለት ዓመት በኋላም ፈርዖን ሕልምን አየ፤ እነሆም፥ በወንዙ ዳር ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ። |
ታስረው የነበሩት የግብጽ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍች ነበረው።
እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ወይም ቃልህን ባይቀበሉ ግን፣ ከአባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ቀድተህ በደረቅ ምድር ላይ አፍስሰው። ከወንዙም ቀድተህ ያፈሰስኸው ውሃ በምድር ላይ ደም ይሆናል።”
እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። “ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ። “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።
ግብጽ ባድማና ምድረ በዳ ትሆናለች፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። “ ‘ “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ እኔም ሠርቼዋለሁ” ብለሃልና፤
በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፣ “በርሱ ምክንያት ዛሬ በሕልም ብዙ ስለ ተሠቃየሁ፣ በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም ነገር እንዳታደርግ” የሚል መልእክት ላከችበት።